Fana: At a Speed of Life!

ብልፅግና ፓርቲ በአርባ ምንጭ ከተማ የምርጫ ቅስቀሳ አካሄደ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ብልፅግና ፓርቲ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ከተማ የምርጫ ቅስቀሳ ማጠቃለያ መርሐ ግብር አካሂዷል።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድርና የብልፅግና ፓርቲ ምክር ቤት አባል ጥላሁን ከበደ በዚህ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት÷ ፓርቲው ባለፉት ስምንት ዓመታት የአፍሪካ የልማት ምሳሌ ማድረጉን ገልጸዋል።
ፓርቲው ከምርጫው ማግስትም ግዙፍ የልማትና የቱሪዝም ፕሮጀክቶችን እንደሚያስቀጥል ጠቅሰው÷ ሕዝቡ ብልፅግና ፓርቲን እንዲመርጥ ጠይቀዋል።
የጋሞ ዞን አስተዳዳሪ ደምስ አድማሱ (ዶ/ር) በበኩላቸው÷ ብልፅግና ፓርቲ ሀገሪቱን ከነበረችበት ውስብስብ ችግር አውጥቶ ወደ ተምሳሌትነት እያሻገራት መሆኑን ጠቅሰዋል።
በዞኑና በከተማው የመንገድ ልማትን ጨምሮ ሁሉን አቀፍ መሠረተ ልማቶች መፈታታቸውን በማንሳት ሕዝቡ ግንቦት 24 በነቂስ ወጥቶ ድምፅ እንዲሰጥ ጥሪ አቅርበዋል።
ምርጫ የዜጎች ሕገ መንግስታዊ መብት መሆኑና ብልፅግና ፓርቲም በበርካታ ፈተናዎች ውስጥ አልፎ ቃሉን በተግባር እያረጋገጠ እንደሚገኝ ተገልጿል።
በአለምሰገድ አሳዬ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.