ፕሬዚዳንት ታዬ ለዒድ አል-አድሃ (ዐረፋ) በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ለ1447ኛው የዒድ አል-አድሃ (ዐረፋ) በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ፡፡
ፕሬዚዳንቱ በመልዕክታቸው መላው የእስልምና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያውያን ለበዓሉ እንኳን በሰላም አደረሳችሁ ብለዋል፡፡
በዓሉ የሰላም፣ የአንድነት፣ የፍቅርና የመተሳሰብ እንዲሆን መልካም ምኞታውን ገልጸዋል፡፡