አቶ አደም ፋራህ ለዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ ለ1 ሺህ 447ኛው የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
አቶ አደም ፋራህ በመልዕክታቸው፤ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1 ሺህ 447ኛው ዓመተ ሂጅራ የአረፋ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን ብለዋል።