Fana: At a Speed of Life!

የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በሀዋሳ ከተማ እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) 1 ሺህ 447ኛው የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በሀዋሳ ከተማ በድምቀት እየተከበረ ነው።

በዓሉ ህዝበ ሙስሊሙ በተገኘበት በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓቶች በሚኒሊየም አደባባይ በሶላት እና በተክቢራ ነው በድምቀት እየተከበረ የሚገኘው።

የሀዋሳ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ሰብሳቢ ሼክ ጀማል አብዱሽኩር ባስተላለፉት መልዕክት፤ ህዝበ ሙስሊሙ እንደ ነብዩ ኢብራሂም ሁሉ ለአሏህ ታማኝ ሆኖ ለችግረኞች በመድረስ በዓሉን ማክበር ይገባዋል ብለዋል።

በጥላሁን ይልማ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.