አሜሪካ በኢራን ላይ የአየር ጥቃት ፈፀመች
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአሜሪካ ጦር ስልታዊ በሆነችው የኢራን የወደብ ከተማ ባንዳር አባስ ወታደራዊ ቦታ ላይ አዲስ ጥቃት ፈፅሟል።
የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ እንዳስታወቀው፥ ጦሩ በሆርሙዝ ሰርጥ አካባቢ ስጋት ፈጥረዋል ያላቸውን አራት የኢራን ድሮኖች አውድሟል።
የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ በበኩሉ፥ የአሜሪካ የአየር ጦር ሰፈርን ኢላማ በማድረግ አጸፋ መውሰዱን ገልጾ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት መቆጠቡን ቢቢሲ ዘግቧል።
የኩዌት ጦር ግን የአየር መከላከያው የጠላት ሚሳኤል እና ሰው አልባ አውሮፕላኖችን እየጠለፈ እና እየተከላከለ እንደነበር ያስታወቀ ሲሆን በትክክል ከየት እንደመጡ አልገለጸም።
አሜሪካ በኢራን ላይ ጥቃት ስትሰነዝር በሦስት ቀናት ውስጥ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው።
ከሁለት ቀናት በፊት አሜሪካ በደቡባዊ ኢራን በሚገኙ የኢራን የሚሳኤል ቤዞች እና ፈንጅ ሲቀብሩ ነበር ባለቻቸው ጀልባዎች ላይ የአየር ጥቃት መፈጸሟ ይታወሳል።
ዳግም የተቀሰቀሰው ጦርነት በአሜሪካ እና በኢራን መካከል የተጀመረውን ጦርነት የማቆም ድርድር ስጋት ውስጥ የከተተው ሆኗል።