የአጀንዳ ማሰባሰብ ሒደቱ ነፃ፣ አካታችና ዲሞክራሲያዊ እንዲሆን ተሰርቷል – ኮሚሽነር መስፍን ዓርአያ (ፕ/ር)
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የአጀንዳ ማሰባሰብ ሒደቱ ነፃ፣ አካታችና ዲሞክራሲያዊ እንዲሆን ተሰርቷል አሉ ኮሚሽነር መስፍን ዓርአያ (ፕ/ር)፡፡
ኮሚሽኑ በምክክር ረቂቅ አጀንዳ ዙሪያ ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችና ማህበራት ጋር እየመከረ ይገኛል፡፡
ኮሚሽነሩ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ በዚህ ዓመት በሚካሄደው የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ላይ 4 ሺህ ተወካዮች ይሳተፋሉ፡፡
በአጀንዳ ማሰባሰብ ሒደቱ 93 በመቶ የሀገሪቱ ወረዳዎች ተደራሽ ሆነዋል ያሉት ኮሚሽነሩ፥ ሒደቱ ነፃ፣ አካታችና ዲሞክራሲያዊ እንዲሆን መሰራቱን ጠቁመዋል፡፡
በዙፋን አምባቸው