Fana: At a Speed of Life!

ፋና ላምሮት ምዕራፍ 22 የፊታችን ቅዳሜ ቀጥሎ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 21 ፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በተወዳዳሪዎች አስደናቂ ብቃት የጀመረው ፋና ላምሮት ምዕራፍ 22 በመጪው ቅዳሜ ከሰባት ተወዳዳሪዎች ጋር ይቀጥላል፡፡

ለሁለት ወራት በተለያየ ምድብ ሲፎካከሩ የነበሩት የምዕራፍ 22 ተወዳዳሪዎች ባለፈው ቅዳሜ መገናኘታቸው ይታወቃል፡፡

ተወዳዳሪዎች ቅዳሜ በዳኞች የሙዚቃ ምርጫ የሚወዳደሩ ሲሆን ÷ ከኮከብ ባንድ ጋር በሁለት ዙር ሥራዎቻቸውን ያቀርባሉ፡፡

በምዕራፉ ፍጻሜ የሚቀሩ 4 ተወዳዳሪዎች የ1 ሚሊየን ብር ሽልማት ተዘጋጅቶላቸዋል፡፡

ለፍጻሜ የሚደርሱ 4 ተወዳዳሪዎች ደግሞ ወደ 6ኛው የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር በቀጥታ የሚያልፉ ይሆናል፡፡

ቅዳሜ በቀጥታ ሥርጭት ልክ 6 ሰዓት ላይ ይጠብቁን!

በለምለም ዮሐንስ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.