Fana: At a Speed of Life!

በፍኖተ ሰላም ከተማ የምርጫ ቁሳቁስ ሥርጭት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 21፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ፍኖተ ሰላም ከተማ የምርጫ ቁሳቁስ ወደ ምርጫ ጣቢያዎች እየተሰራጨ ይገኛል፡፡

የምርጫ ክልሉ አስተባባሪ መለሰ ጌታነህ እንደገለፁት÷ በፍኖተ ሰላም የምርጫ ክልል 89 የምርጫ ጣቢያ አለ፡፡

ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ለሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ የመራጮች የድምጽ መስጫ አስፈላጊ ቁሳቁስ በመሰራጨት ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

የምርጫ አሥፈፃሚዎች በሙሉ ዝግጁነት ቁሳቁሱን እየተረከቡ እንደሆነ ጠቅሰው፤ ዛሬ የጀመረው የቁሳቁስ ሥርጭት ነገም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መጠቆማቸውን የከተማዋ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.