Fana: At a Speed of Life!

ታዛቢዎች ባሰማራንባቸው ጣቢያዎች 99 በመቶ ያህሉ ያለገደብ ምርጫውን ታዝበዋል – ህብረት ለምርጫ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ህብረት ለምርጫ ታዛቢዎች 99 በመቶ ያለምንም ገደብ ወደ ድምጽ መስጫ ጣቢያዎች ገብተው መታዘብ ችለዋል አለ።

የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ህብረት ለምርጫ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ እስከ ቀን 7 ሰዓት ያሉትን የትዝብት ግኝቶችን ብቻ ለመገናኛ ብዙሃን ይፋ አድርጓል።

ህብረት ለምርጫ በመግለጫው፤ ለምርጫው 2 ሺህ 258 ተቀማጭ እና 891 ተንቀሳቃሽ በአጠቃላይ 3 ሺህ 149 ታዛቢዎችን ከማለዳው 11 :30 ጀምሮ በ2 ሺህ 258 ድምፅ መስጫ ጣቢያዎች ላይ አሰማርቶ እየታዘበ እንደሆነ ገልጿል።

በዚህም እያንዳንዱ ታዛቢ ቢያንስ 6 ጣቢያዎችን እንዲታዘብ መሰማራታቸውንና ታዛቢዎች 99 በመቶ ያለምንም ገደብ ወደ ድምጽ መስጫ ጣቢያዎቹ ገብተው መታዘብ መቻላቸውን አስታውቋል።

ታዛቢዎች ከተሰማሩባቸው 2 ሺህ 258 ጣቢያዎች ውስጥ 2 ሺህ 183 የምርጫ ጣቢያዎች ወይም 97 በመቶ ያህሉ የህብረቱ ታዛቢዎች በስፍራው ሲደርሱ የምርጫ አስፈፃሚዎች በቦታው እንደነበሩ አስረድቷል።

ኅብረቱ ከታዘባቸው 2 ሺህ 258 የድምፅ መስጫ ጣቢያዎች መካከል በ947 (42 በመቶ) ጣቢያዎች የድምፅ መስጠት ሂደቱ ከማለዳ 12 ሰዓት በፊት መጀመሩንና በ1 ሺህ 276 (57 በመቶ ) ጣቢያዎች ደግሞ ከማለዳ 12 እስከ 1 ሰዓት ባለው ጊዜ መጀመሩን ታዝቧል።

በተቃራኒው 32 (1 በመቶ ) ጣቢያዎች የድምፅ አሰጣጥ ከጠዋቱ 1 ሰዓት በኋላ መጀመሩንና በ3 ጣቢያዎች ይህ መግለጫ እስከተዘጋጀበት ሰዓት ድረስ የድምፅ አሰጣጥ ሂደት እንዳልተጀመረ መታዘቡን አመላክቷል።

በምንተስኖት ሙሉጌታ

#ኢትዮጵያ #ኢትዮጵያእየመረጠችነው #በምርጫብቻ #ፋናዲጂታል #Election #fanadigital #Ethiopia #Ethiopiavotes #Democracy #fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.