Fana: At a Speed of Life!

የአርሶ አደሩን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማሳድግ በትኩረት ይሰራል – አቶ ደስታ ሌዳሞ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሲዳማ ክልል የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥና የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማሳድግ በቁርጠኝነት ይሰራል አሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ ።

የሲዳማ ክልል የ2018/19 ምርት ዘመን የመኸር እርሻ ንቅናቄ መርሐ ግብር በሀዋሳ ከተማ እየተካሄደ ነው።

አቶ ደስታ ሌዳሞ በዚህ ወቅት እንዳሉት፥ በክልሉ የምግብ ዋስትናን የሚያረጋግጡና ገበያን የሚያረጋጉ የግብርና ልማት ሥራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ።

የግብርና ምርታማነቱን ለማሳካት ከበልግ ምርት መሰብሰብ ጎን ለጎን የመኸር ሰብልን ውጤታማ ለማድረግ በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል።

የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥና የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማሳድግ በሚከናወኑ ሥራዎች ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ መምሩ ሞኬ በበኩላቸው ፥ በዘንድሮው መኸር ከ169 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በተለያዩ ሰብሎች ይለማል ብለዋል።

በምርት ዘመኑ ከ16 ነጥብ 5 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት እንደሚጠበቅና ለዚህም ዝግጅት እየተደረገ ነው ማለታቸውን የርዕሰ መስተዳድሩ ጽ/ቤት የዲጂታል ቴክኖሎጂና ሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ቴዎድሮስ ታደሰ ለፋና ዲጂታል ገልጸዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.