Fana: At a Speed of Life!

100 ሺህ ወጣቶችን የሥራ ዕድል ተጠቃሚ የሚያደርግ ፕሮግራም ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር “ብቃት” የተሰኘ 100 ሺህ ወጣቶችን የሥራ ዕድል ተጠቃሚ የሚያደርግ ፕሮግራም ይፋ አድርጓል።
ሚኒስቴሩ የወጣቶችን የሥራ አጥነት ችግር ለመፍታት ከዓለም ባንክ ጋር በመተባበር “ብቃት’” የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮግራምን በ11 ከተሞች ሲተገብር ቆይቷል፡፡
አሁን ላይም ይህንን የሥራ ዕድል ወደ 16 ከተሞች በማስፋት 100 ሺህ ተጨማሪ ወጣቶችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ፕሮግራም ነው ይፋ ያደረገው፡፡
ፕሮግራሙ በዓለም ባንክ 52 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ በሚቀጥሉት 2 ዓመታት የሚተገበር ሲሆን÷ ከ18 እስከ 29 የዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ወጣቶችን ተጠቃሚ ያደርጋል፡፡
በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴዔታ ሰለሞን ሶካን ጨምሮ የክልሎች የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
በፌቨን ቢሻው
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.