በኢትዮጵያ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን ተደራሽነት ለማስፋት..
በኢትዮጵያ የሁሉንም ብራንዶች እና ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ተደራሽነት ይበልጥ ለማጠናከር በትኩረት እየሰራሁ ነው አለ ቴክ ኢዚ፡፡
ቴክ ኢዚ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን በአንድ ቦታ እና በተመጣጣኝ ዋጋ ማግኘት የሚቻልበትን ሱቁ ዛሬ በአዲስ አበባ መገናኛ አካባቢ በሚገኘው ቤተልሄም ፕላዛ በይፋ ከፍቷል፡፡
ይህም ሕብረተሰቡ ሁሉንም አይነት የመገልገያ ምርቶች እንዲሁም የሁሉንም ብራንድ አይነቶች በአንድ ቦታ ያለምንም እንግልት በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኝ ያስችላል፡፡
ማዕከሉ ቴክ ኢዚ በኢትዮጵያ ለሚያደርገው ረጅም ጉዞ ትልቁን ድርሻ የሚጫወት ሲሆን ÷ በቅርቡም በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በሰፊው ሱቆቹን የማስፋፋት እቅድ እንዳለው ተመላክቷል፡፡
ቴክኢዚ በሱቆቹ ከቴክኖ ጀምሮ የአፕል፣ ሚዲያ፣ ኢንፊኒክስ እና ሌሎችንም ብራንድ ምርቶች በአንድ የሚያካትት ይሆናል፡፡
በመክፈቻ መርሐ ግብሩ የሚመለከታቸው የንግዱ እና የመንግስት አካላት፣ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ፣ ሸማቾች እና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
የአዲሱ ሱቅ የጉብኝት መርሐ ግብር በቴክኢዚ የተካተቱ ምርቶች ማሳያ እና የመዝናኛ ፕሮግራሞች በመክፈቻ ሥነ ሥርዕቱ የተካተቱ ናቸው፡፡
የብራንዱ የኢትዮጵያ ተጠሪዎች በፕሮግራሙ ቴክኢዚ በኢትዮጵያ በሸማቹ ታማኝ የሆነ፣ በዋጋ የሚመረጥ እና ሁሉንም በአንድ የሚያገኙበት ጠንካራ ብራንድን መገንባት አላማው እንዳደረገ ተናግረዋል፡፡
ሸማቾች የትኛውንም መገልገያ ከቴክ ኢዚ ሱቆች ሲገዙ የሚፈልጉበት ቦታ ድረስ ማድረስና የገዟቸው የኤሌትሮኒክስ መገልገያዎች ብልሽት በሚያጋጥሟቸው ወቅት ደረጃውን በጠበቀ መልኩ የጥገና ስራ መስጠት የሚያስችል ቡድን እና ማዕከል ማዘጋጀቱም ተጠቁሟል፡፡
በተጨማሪም ቴክ ኢዚ በይፋ ስራ መጀመሩን ምክንያት በማድረግ የተለያዩ አጓጊ ዕድሎች እና ፓኬጆችን ለሸማቹ ማሕበረሰብ ይፋ ማድረጉን የተቋሙ መረጃ ያመላክታል፡፡