Fana: At a Speed of Life!

የአገልግሎቱን ሰነዶች ወደ ዲጂታላይዜሽን ለማሸጋገር የሚያስችል ዳታ ቤዝ ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት ሰነዶችን ወደ ዲጂታላይዜሽን ለማሸጋገር የሚያስችል ዳታ ቤዝ ይፋ ተደርጓል፡፡
የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ አገልግሎቱ የኢትዮጵያውያንን ባህል፣ ወግ፣ ስነ ጽሁፍና ፍልስፍና ሰንዶ በማቆየት ጉልህ አስተዋጽኦ አበርክቷል፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) በበኩላቸው÷ እንደ ሀገር ተቋማትን ወደ ዲጂታላይዜሽን ለማሸጋገር ሰፊ ስራ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
የቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት በርካታ እውቀቶችን ለቀጣይ ትውልድ ከማስተላለፍ አንፃር የላቀ ሚና እንዳለው አንስተዋል፡፡
የቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት የሀገሪቱን ታሪካዊ ሰነዶች፣ ብርቅዬ መጻሕፍትና ቅርሶች በማሰባስብ፣ በማደራጀትና ለሕዝብ ተደራሽ በማድረግ ጠንካራ ስራ ሲሰራ ቆይቷል ያሉት ደግሞ የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ሰርፀ ፍሬስብሃት ናቸው፡፡
በዛሬው ዕለት ይፋ የተደረገው ዳታ ቤዝ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ከ126 ሚሊየን በላይ በሆነ ወጪ የተዘጋጀ መሆኑም ተመላክቷል፡፡
በታምራት ደለሊ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.