Fana: At a Speed of Life!

የአርቲስት ሰማኸኝ በለው ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አንጋፋው የባሕል ሙዚቃ አቀንቃኝ አርቲስት ሰማኸኝ በለው (ሰሜ ባላገሩ) ሥርዓተ ቀብር በዛሬው ዕለት ተፈጽሟል፡፡

ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው ባደረበት ሕመም በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ በትናንትናው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡

ድምጻዊው ለሕዝብ ካበረከታቸው የሙዚቃ ሥራዎች መካከል ነይ ዘመድዬ፣ እንዴት ነሽ፣ ደቦት እንስራ፣ ዘና በይ፣ ባላገር እና ሌሎች ይገኙበታል፡፡

ሥርዓተ ቀብሩ ቤተሰቦቹ፣ ወዳጅ ዘመዶቹና አድናቂዎቹ በተገኙበት በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ቡልቡላ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ተፈጽሟል፡፡

በዐምደወርቅ ሽባባው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.