Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል ለአረንጓዴ ዐሻራ 1 ነጥብ 78 ቢሊየን ችግኞች ተዘጋጅተዋል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል ለ2018 የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር 1 ነጥብ 78 ቢሊየን ችግኞች ተዘጋጅተዋል አለ የክልሉ ግብርና ቢሮ።
የቢሮው ም/ኃላፊ መሰሉ ብርሃኑ እንዳሉት÷ በክልሉ ባለፉት ዓመታት በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር የተተከሉ ችግኞች ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አስገኝተዋል፡፡
የ2018 ዓ.ም የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብርን በስኬት ለማጠናቀቅም አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት መደረጉን አመልክተዋል፡፡
ካለፈው ዓመት ልምድ በመውሰድ ለደንና ፍራፍሬ ልማት የሚውሉና ገቢ ሊያስገኙ የሚችሉ የችግኝ አይነቶችን በመለየት ወደ ሥራ መገባቱን አስረድተዋል።
አሁን ላይም በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች 1 ነጥብ 78 ቢሊየን የጥምር ደን፣ የቡና፣ የፍራፍሬና ሌሎች የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ የሚያስችሉ ችግኞች መዘጋጀታቸውን አብራርተዋል፡፡
በተጨማሪም ለችግኝ መትከያ ቦታዎች የካርታ እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን የማዘጋጀት ሥራ መከናወኑን ነው የገለጹት፡፡
በዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር የታቀደውን ሥራ በስኬት ለማጠናቀቅ የክልሉ ሕዝብ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርግም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በዮናስ ጌትነት
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.