ዓለም አቀፋዊ ትስስርን በማሳለጥ የኢትዮጵያን የልማት መናኸሪያነት የሚያረጋግጠው አውሮፕላን ማረፊያ…
👉 የቢሾፍቱ አቡሴራ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክት ቢሾፍቱን፣ ሞጆን፣ ዱከምንና አዲስ አበባን የሚያስተሳስር አዲስ የኢኮኖሚ ኮሪደር ይፈጥራል።ይህ ከተሞች፣ የንፁህ ውሃ አቅርቦት፣ የኃይል እና የመገናኛ መሠረተ ልማቶችን በጥራት እንዲያድጉ ያደርጋል።
👉 አውሮፕላን ማረፊያው የዓለም አቀፍ አየር መንገዶች መዳረሻነት እድልን ይዞ ይመጣል፡፡ በዓመት እስከ 110 ሚሊየን መንገደኞችን የማስተናገድ አቅም የሚኖረው በመሆኑ፣ ከእስያ፣ ከአውሮፓ፣ ከአሜሪካ እና ከላቲን አሜሪካ የሚነሱ ተያያዥ በረራዎችን በአንድ ማዕከል ያስተናግዳል ፤ ይህም ግዙፍ የመንገደኞች ፍሰትን ይፈጥራል፡፡
👉 የኢትዮጵያ አየር መንገድ አባል የሆነበት ስታር አሊያንስ እና ሌሎች ዓለም አቀፍ አየር መንገዶች አቡሴራን ዋና የምስራቅ አፍሪካ መሸጋገሪያ መናኸሪያቸው ያደርጉታል። የአሊያንስ ማዕከልነታችንንም የምናረጋግጥበት ይሆናል፡፡
👉 የግሎባል ደቡብ ዋነኛ ትስስር ድልድይ ሆኖ ያገለግላል፡፡ አዲሱ ማረፊያ አፍሪካን ከላቲን አሜሪካ፣ ከእስያ (በተለይም ከቻይና እና ህንድ) እና ከመካከለኛው ምስራቅ ጋር በቀጥታና በአጭር ሰዓት የሚያገናኝ ዋነኛ መስመር ይሆናል። ይህ ሲሆን ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን አፍሪካን ከዓለም ጋር አስተሳሰርን ማለት ነው፡፡
👉 የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነትን ተፈፃሚነት ለማፋጠን ሰዎችንና የንግድ ዕቃዎችን ከአህጉሪቱ ጥግ እስከ ዓለም ጫፍ በፈጣን የሎጂስቲክስ ሰንሰለት ያገናኛል። ለአህጉር አቀፍ ንግድ መነቃቃት አበርክቶው ከፍተኛ ይሆናል፡፡
👉 ፕሮጀክቱ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ያላትን ስልታዊ፣ ፖለቲካዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ተሰሚነት ያጠናክራል፡፡ የሀገሪቱን የኢኮኖሚ እድገትም በከፍተኛ ፍጥነት የሚያሳልጥ ታላቅ ብሔራዊ ፕሮጀክት ነው።