በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ተጀመረ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በጋሞ ዞን አርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ የዘንድሮውን አረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር አስጀምረዋል።
በክልሉ በ2018 ዓ.ም የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ከ500 ሚሊየን በላይ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች ለተከላ ዝግጁ መደረጋቸው ተመላክቷል።
የዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ በክልሉ በሁሉም አካባቢዎች ተጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን ÷ የሚተከሉ ችግኞች ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው መሆናቸው ተጠቁሟል።
“ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ሃሳብ በተጀመረው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር የክልሉ ሕዝብ በንቃት እንዲሳተፍ ጥሪ ቀርቧል፡፡
በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ አቶ ጥላሁን ከበደን ጨምሮ የክልሉ ም/ቤት ዋና አፈ ጉባዔ አለማየሁ ባውዲ፣ ም/ርዕሰ መስተዳድር አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) እና ሌሎች አመራሮች ተገኝተዋል፡፡