Fana: At a Speed of Life!

በዴራ እና ኢትያ ከተሞች የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጠት ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ዴራ እና ኢትያ ከተሞች የተገነቡ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ በዛሬው ዕለት በይፋ ሥራ ጀመረ።

የዞኑ አስተዳዳሪ ኢብራሂም ከድር በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ በዞኑ በሚገኙ ሌሎች ከተሞችም አገልግሎቱን ለማስፋፋት እየተሰራ ይገኛል፡፡

በዛሬው ዕለት ለአገልግሎት ክፍት የተደረጉት ማዕከላት የሕዝብን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመመለስ ትልቅ አቅም እንደሚሆኑ አንስተዋል።

በከተሞቹ አገልግሎት አሰጣጥን ለማቀላጠፍ ዘመናዊና የተቀናጀ ሥርዓት መዘርጋቱ እንግልትን የሚያስቀር በመሆኑ መደሰታቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል።

ቀደም ሲል አንድን ጉዳይ ለማስፈጸም ከተለያዩ መሥሪያ ቤቶች መመላለስና መጉላላት የተለመደ እንደነበር አስታውሰው፥ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መጀመሩ ከእንግልትና ካልተገባ ወጪ የሚታደግ መሆኑን ገልጸዋል።

በኦሊያድ በዳኔ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.