የቬንዙዌላ የርዕደ መሬት አደጋ ተጎጂ ከ8 ቀናት በኋላ በሕይወት ተገኘ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በቬንዙዌላ የርዕደ መሬት አደጋ ጉዳት ከደረሰበት ሕንፃ ፍርስራሽ ውስጥ ከስምንት ቀናት በኋላ ጊል ከጋሌሪያስ ፕላያ ግራንዴ የተባለ ሰው በሕይወት ተገኝቷል
የኮስታሪካ ቀይ መስቀል ፓራሜዲክ ባለሙያ አለን ማድሪጋል እንደገለጹት፤ አደጋው በተከሰተ ጊዜ ግለሰቡ የገበያ ማዕከል አጠገብ ባለው የመኪና ማቆሚያ ክፍል ውስጥ ተረኛ ሰራተኛ ነበረ።
ተጎጂው ባለፈው እሁድ ድምጽ ማሰማቱን ተከትሎ የነፍስ አድን ሰራተኞች ህይወት ለማዳን ብርቱ ጥረት አድርገዋል።
የህንጻው መተላለፊያዎች በአደጋው በመውደማቸው ነፍስ የማዳን ስራው ለአደጋ ሰራተኞችች በጣም ውስብስብ እና አስቸጋሪ እንደነበር የተናገሩት አለን ማድሪጋል፤ አስቸጋሪ ሁኔታውን በማለፍ ሄርናን ጊልን በህይወት ማውጣት ተችሏል ብለዋል።
እስከ ሐሙስ ምሽት ድረስ በአደጋው ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 2 ሺህ 595 የደረሰ ሲሆን፤ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ደግሞ እስካሁን የደረሱበት አለመታወቁን ቢቢሲ ዘግቧል።
በትዕግስት ግዛቸው