የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 30ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ(ዶ/ር) ከምክር ቤቱ አባላት ለተሱላቸው ጥያቄዎች የሰጡት ዋና ዋና ማብራሪያዎች፡ On Jul 7, 2026 76 የዘንድሮ ምርጫ ለመማር ፈቃድ ላለው ለየትኛውም የፖለቲካ አካል ትልቅ ትምህርት የሰጠ ዘርፈ ብዙ መልእክቶች የያዘ የኢትዮጵያን ህዝብ እንቆቅልሽ፣ የህዝቡ እምነት በምን ያህል ደረጃ የተለያየ መሆኑን ያየንበት ነው። አትደግፉ፣ አትምረጡ፣ አትመዝገቡ ተብለው ህዝቡ ማሥፈራሪያዎቹን ሳይቀበል በነቂስ ወጥቶ እስካሁን ታይቶ የማይታወቅ ህዝብ ተመዝግቦ በሌሊትም የመረጠበት ነው። በምርጫው የኢትዮጵያን ህዝብ ተሳትፎ ማየት የቻልንበት ሂደት ነበር፤ ምርጫው ከእስካሁኖቹ ምን ይለየዋል ካላችሁ ከዚህ ቀደም የሚፎካከሩ ሃይሎች፣ በሃሳብ አልፎ አልፎም በጉልበት ይጠቃቃሉ ዘንድሮ ግን እራሱ ምርጫው የጥቃት ዒላማ ነበር። የኛን ባንዳዎች የሚያሰማሩ ሃይሎች በሙሉ ምርጫ አይወዱም፤ በዚህም ምርጫውን የጥቃት ዒላማ አድርገውት ነበር። ማሸነፍ፣ ከፈተና መሻገር፣ ችግሮችን በብልሃት የማለፍና ሀገር የማጽናት ልምድ ያለው የኢትዮጵያ ህዝብ እነዚያን ፍላጎቶች ሳይቀበል በተባበረ ክንድ ላደረገው አስተዋጾኦ ክብር ይገባዋል። ሰው እየደከመ እየሰነፈ ሲሄድ ኩራት እና ፉከራ ያበዛል በዘንድሮው ምርጫ አትችሉም፣ አይሳካም የሚል ሃሳብ የብዙ ኃይሎች ፍላጎት ቢሆንም ኢትዮጵያውያን ጽንፈኝነት፣ ዘረኝነት፣ ባንዳነት አንፈልግም የሚለውን እኛ ተባብረን የጋራ ሀገር ማጽናት ማበልጽግ ነው የሚለውን በጋራ አስተጋብተናል። ደቡብ፣ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ምስራቅ ብትሄዱ አንድ ድምጽ ነበር እሱም ጽንፈኝነት፣ ባንዳነት አንፈልግም የሚል ነበር። አረጋውያን መርጠዋል እነሱ የመረጡት በእነሱ ድምጽ ሀገር መጽናት ስላለበት ነው። ሃዘንተኞች፣ እናቶች ልጆች አዝለው፣ ህመምተኞች ወጥተው መርጠዋል ከዚህ ባሻገር የጥይት ድምጽ እየሰሙ ሸብረክ ሳይሉ የመረጡ ዜጎችም አሉ። ለተመረጠው መንግሥት ሰው እና በከፍተኛ ሁኔታ አደራ የሰጡ ሲሆን እኛም በታላቅ ሸክም፣ ሃላፊነት የምናየው ይሆናል። በሶስና አለማየሁ 76 Share FacebookTwitterTelegramWhatsAppEmailViberPrint