Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ የኢራን ወታደራዊ ኢላማዎች ላይ ጥቃት ሰነዘረች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢራን በሆርሙዝ ሰርጥ የሚተላለፉ የንግድ መርከቦች ላይ ጥቃት ፈጽማለች በሚል አሜሪካ በአንድ ሌሊት በርካታ የኢራን ወታደራዊ ኢላማዎች ላይ ጥቃት መፈጸሟን አስታወቀች።

የአሜሪካ ጦር የሆርሙዝ ሰርጥ ለዓለም አቀፍ ንግድ ወሳኝ መተላለፊያ በመሆኑ ኢራን እንድትቆጣጠረው የማይፈቅድ መሆኑን ገልጿል።

ኢራን ለተሰነዘረው ጥቃት በሰጠችው አጸፋ በዮርዳኖስ፣ ባህሬን እና ኩዌት የሚገኙ የአሜሪካ ጦር ሰፈሮችን እንዲሁም በኦማን የሚገኙ የራዳር መቆጣጠሪያዎች ላይ ጥቃት መፈጸሟን ጠቁማለች።

የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ባለፈው ሳምንት ከኢራን ጋር ተደርሶ የነበረው የተኩስ አቁም ስምምነት አብቅቷል ማለታቸውን ተከትሎ ዳግም ባገረሸው ጦርነት አሜሪካ ኢራን ላይ ለሶስተኛ ጊዜ ጥቃት ፈጽማለች፡፡

የኢራን ከፍተኛ ተደራዳሪ ሙሀመድ ባግር ከድርድሩ ጋር ተያይዞ በኤክስ ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ አሜሪካ ቃሏን ካልጠበቀች ዋጋ ትከፍላለች ብለዋል።

በጦርነቱ ሳቢያ የተዘጋው የሆርሙዝ ሰርጥ የሀገራትን የንግድ እንቅስቃሴ እያስተጓጎለ ነው፡፡

ቀውሱ በማገርሸቱ የአንድ በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ 79 ዶላር የደረሰ ሲሆን፤ ይህም ከዳግም ግጭቱ በኋላ በከፍተኛ ሁኔታ ማሻቀቡን ቢቢሲ ዘግቧል

በእመቤት ሲሳይ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.