Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከቤኒን ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቤኒን ፕሬዚዳንት ሮሙዋልድ ዋዳግኒ ጋር ተወያይተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷ የቤኒን ፕሬዚዳንት ሮሙዋልድ ዋዳግኒን ተቀብዬ በወል ጉዳዮች ዙሪያ መክረናል ብለዋል።

‎በውይይቱም የሁለትዮሽ ግንኙነት ማጠናከር እና በጋራ ጥቅሞች ላይ የላቀ ትብብር ለማድረግ በሚያስችሉ ዕድሎች ዙሪያ ፍሬያማ ምክክር አድርገናል ነው ያሉት፡፡

ሁለቱ ሀገራት ለጥልቅ አጋርነት እና ለዘላቂ ወዳጅነት ያላቸውን የጋራ ቁርጠኝነት ይበልጥ ለማሳደግ ጽኑ ፍላጎት እንዳላቸውም አመልክተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.