ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከአውሮፓ ሕብረት የውጭ ጉዳይና ደህንነት ፖሊሲ ከፍተኛ ተወካይ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአውሮፓ ሕብረት የውጭ ጉዳይና ደህንነት ፖሊሲ ከፍተኛ ተወካይ ካያ ካላስ ጋር ተወያይተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷ የአውሮፓ ሕብረት የውጭ ጉዳይና የደህንነት ፖሊሲ ከፍተኛ ተወካይ ካያ ካላስን ዛሬ ተቀብዬ ፍሬያማ ውይይት አድርገናል ብለዋል።
በውይይታቸውም በአውሮፓ ሕብረት እና አፍሪካ መካከል ያለውን ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መምከራቸውን ጠቅሰዋል፡፡
በጋራ ጥቅሞች እና ቅድሚያ በሚሰጣቸው ቁልፍ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ሃሳብ ተለዋውጠናል ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)።
ትኩረት የሚሹና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ መሰረት ባደረገው ውይይት ኢኮኖሚያዊ ትብብርን ይበልጥ ለማሳደግና ለማስፋፋት በሚያስችሉ መንገዶች ላይ መምከራቸውንም ጠቁመዋል፡፡