Fana: At a Speed of Life!

ኮርፖሬሽኑ ከ750 ሚሊየን ዶላር በላይ ኢንቨስትመንት ሳበ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በ2018 በጀት ዓመት ከ750 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ ኢንቨስትመንት ስቧል።

የኮርፖሬሽኑ የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በሐዋሳ ከተማ እየተገመገመ ይገኛል፡፡

በመድረኩ የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር)÷በበጀት ዓመቱ ከ750 ሚሊየን ዶላር በላይ የሚገመት ኢንቨስትመንት ያላቸው 166 ባለሃብቶችን በልዩ የኢኮኖሚ ዞኖችና ኢንዱስትሪ ፓርኮች ተሰማርተዋል ብለዋል።

ከተሳቡት ኢንቨስትመንቶች መካከል 84 በመቶ የሀገር ውስጥ፣ 10 በመቶ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት እንዲሁም ቀሪው 6 በመቶ ደግሞ የሀገር ውስጥና የውጭ ባለሃብቶች ጥምረት መሆኑን አብራርተዋል።

የቻይና፣ አሜሪካ፣ እንግሊዝ፣ ህንድ እና ጅቡቲ ባለሃብቶች በኢንዱስትሪ ፓርኮች እና ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ከተማሰሩ ኩባንያዎች ውስጥ እንደሚገኙበት መጥቀሳቸውን የኮርፖሬሽኑ መረጃ አመልክቷል።

ኢንቨስትመንቶቹ በንግድና ሎጂስቲክስ፣ በአግሮ ፕሮሰሲንግ፣ በፋርማሲዩቲካልና በሕክምና መሣሪያ ማምረቻ፣ በአልባሳትና ጨርቃ ጨርቅ፣ በኬሚካልና ኮንስትራክሽን እንዲሁም በኢንጂነሪንግና ብረታ ብረት ዘርፎች የተሰማሩ ባለሃብቶች መሆናቸውን ጠቁመዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.