የኦሮሚያ ክልል የ2019 በጀት 704 ቢሊየን ብር ሆኖ ጸደቀ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጨፌ ኦሮሚያ በአዳማ ከተማ እያካሄደ ባለው 11ኛ መደበኛ ጉባዔው የክልሉን የ2019 በጀት 704 ቢሊየን ብር አድርጎ በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል፡፡
ጨፌው ለ2018 የሥራ ዘመን የሚውል 84 ቢሊየን ብር ተጨማሪ በጀትም በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡
የጨፌ ኦሮሚያ አፈጉ ባኤ ሰዓዳ አብዱረህማን፥ የጸደቀውን በጀት ለሚፈለገው ዓላማ በተገቢው መንገድ ማዋል ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።
በጸሃይ ጉሉማ