የክረምት በጎ ፈቃደኞች በጅማ ደም ለገሱ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በጅማ ከተማ የሚገኙ የክረምት የማህበረሰብ አገልግሎት በጎ ፈቃደኞች የደም ልገሳ ፕሮግራም አካሄዱ፡፡
የሰላም በጎ ፈቃድ የክረምት የማህበረሰብ አገልግሎት የንቅናቄ ፕሮግራም በጅማ ከተማ በተለያዩ ሁነቶች እየተካሄደ ነው፡፡
የሰላም በጎ ፈቃድ የክረምት የማህበረሰብ አገልግሎት የንቅናቄ ፕሮግራም ከሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በሀገራችን በሚገኙ ሃምሳ ከተሞች እየተከናወነ ይገኛል፡፡
ፕሮግራሙ በማህበረሰቡ ውስጥ የቆየውን የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እሴቶቸን በቅንጅት በመምራት በዘላቂነት በጎፈቃደኝነትን ባህል ለማድረግ የታሰበ ነው፡፡
በተጨማሪም ንቅናቄው የማህበረሰቡን ተሳትፎ በማሳደግ ሰላምን፣ አብሮነትን፣ ትብብርን እና ማህበራዊ ትስስርን በማጠናከር ኅብረ-ብሔራዊ አንድነትን ማጎልበት ትኩረት ማድረጉን ከሰላም ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡