Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ዘላቂ የጤና ፋይናንስ ማሻሻያ ላይ ያላቸውን አጋርነት ለማጠናከር ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ዘላቂ የጤና ፋይናንስ ማሻሻያ ላይ ያላቸውን አጋርነት ለማጠናከር ተስማምተዋል፡፡
የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ ከተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ዋና ጸሐፊ አቶ ክላቨር ጋቴቴ ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡
አቶ አህመድ ሺዴ በውይይቱ ወቅት አንዳሉት፤ ኢትዮጵያ ዘላቂ የጤና ፋይናንስ ማሻሻያ ፕሮገራምን ቀድመው ተግባራዊ ከሚያደርጉ አራት ሀገራት አንዷ ያደርጋታል።
የታቀደው ለውጥ ወቅታዊ ከመሆኑም በላይ ለማህበራዊ አገልግሎቶች አዳዲስ የፋይናንስ አማራጮችን ለመለየት መንግስት ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ጉዳዮች ጋር በቅርበት የተሳሰረ ነው ብለዋል፡፡
ሁለቱም ወገኖች የጤና ፋይናንስን እንደ ማህበራዊ ወጪ ብቻ ከመመልከት ይልቅ በሰው ኃይል ልማት፣ በምርታማነት እና በኢኮኖሚ እድገት ላይ የሚደረግ ኢንቨስትመንት አድርጎ መመልከት እንደሚያስፈልግ አጽንኦት ሰጥተዋል።
በተጨማሪም የጤና ዘርፍ ፋይናንስ አቅርቦትን ለማጠናከር የሚያስፈልጉትን የትንተና ሥራ፣ የፖሊሲ ውይይትና የማስተባበር ሥራዎች በጋራ ለመምራት ዝግጁ መሆናቸውንም አረጋግጠዋል፡፡
የኢትዮጵያን ተሞክሮ ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት እንደ ምሳሌ ለማስቀመጥ የሚያስችል የጋራ ቡድን ለማቋቋም መስማማታቸው ተመላክቷል፡፡
በአብረሃም አበራ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.