የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አመራሮችና ሠራተኞች አረንጓዴ ዐሻራቸውን አኖሩ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሠራተኞች አረንጓዴ ዐሻራቸውን አኑረዋል፡፡
የተቋማቱ ሠራተኞች ”ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ሃሳብ ነው በቢሾፍቱ አካባቢ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ያካሄዱት፡፡
በመርሐ ግብሩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስን (ዶ/ር) ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የጎረቤት ሀገራት አምባሳደሮችና የዳያስፖራ አባላት ተሳትፈዋል፡፡
በዚህም አቮካዶ፣ ፓፓያ እና ሌሎች የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ የሚያስችሉ ችግኞች ተተክለዋል፡፡
ኢትዮጵያ እያከናወነች የምትገኘው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ለቀጣናው የጋራ ብልጽግና የነገ ተስፋ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡