Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ በፍጥነት እያደገ የመጣው የዲጂታል ኢኮኖሚ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚን ለመገንባት በመንግሥት፣ በግሉ ዘርፍ እና በአጋር ተቋማት የተለያዩ ጥረቶች እየተደረጉ ይገኛሉ።
ቴክኖሎጂን በመጠቀም ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎችን ለማሳደግ እና አገልግሎቶችን ለማዘመን በተለያዩ ዘርፎች በርካታ ሥራዎች ተከናውነዋል፡፡
የዲጂታል ክፍያ መስፋፋት፣ የሞባይል ባንኪንግ ማደግ እና የኦንላይን ክፍያ አገልግሎቶች በስፋት ጥቅም ላይ እየዋሉ ሲሆን፤ የመንግሥት የዲጂታል አገልግሎቶች በኢንተርኔት ተደራሽ ሆነዋል፡፡
ባለፉት ዓመታት የመደመር መንግሥት የኢ-ኮሜርስ እድገት እንዲፋጠን እንዲሁም የቴክኖሎጂ ስታርትአፖች በተለይም በግብርና፣ በጤና እና በትምህርት ዘርፎች አዳዲስ ድርጅቶች እንዲቋቋሙ በማስቻል ሰፊ ስራዎችን ሰርቷል፡፡
በኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚን ለመገንባት በመንግሥት፣ በግሉ ዘርፍ እና በአጋር ተቋማት የተለያዩ ጥረቶች እየተደረጉ ሲሆን፤ በዚህም መንግሥት የዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂን በመንደፍ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ በቴክኖሎጂ ለማዘመን የብሔራዊ ስትራቴጂ አዘጋጅቶ በትግበራ ላይ አውሏል።
የቴሌኮም ዘርፉን ለውድድር መክፈትና የኢንተርኔት አገልግሎትን በማስፋፋት ረገድ ዘርፍ ብዙ ተግባራት ተከናውነዋል፡፡
የዜጎችን መለያ በዲጂታል ለማስተዳደር ሥርዓት ተዘርግቶ ሚሊየኖች የዲጂታል መታወቂያ ባለቤት ሆነዋል፤ ይህም የፋይናንስ፣ የመንግሥት እና ሌሎች አገልግሎቶችን ቀላል ለማድረግ ይረዳል።
ወጣቶች የቴክኖሎጂ ሥራዎችን እንዲጀምሩ የሚያግዙ የኢኖቬሽን ማዕከላት፣ የሥልጠና ፕሮግራሞች እና የፋይናንስ ድጋፎች እየተስፋፉ ነው።
በሀገሪቷ ያሉ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግና ቴክኖሎጂውን ለማስረጽ ድርሻቸውን ወስደው መንግሥትና የግሉን ዘርፍ ለማገዝ በመስራት ላይ ናቸው፡፡
ዲጂታላይዜሽንን ለማስረጽ በቴሌኮም ዘርፉ እየተወሰደ ያለው እርምጃ የሚበረታታ ነው፡፡
በፋይናንስ ፖሊሲ እየታዩ ያሉ አበረታች ለውጦች፣ የካፒታል ገበያ መቋቋሙና የውጭ ኢንቨስትመንት ማበረታቻዎች መጠናከር ወጣቶች በፈጠራ የታገዘ የኢኮኖሚ ግንባታ ላይ እንዲሳተፉ ያስችላቸዋል።
ዲጂታል ኢትዮጵያ የመንግሥት፣ የግሉን ዘርፍና የልማት ኤጀንሲዎችን በአንድ ላይ በማሰባሰብ የሀገሪቷን የዲጂታል ጉዞ ከአህጉሪቱ ስትራቴጂ ጋር በማስተሳሰር ለማሳለጥ ከፍተኛ ፋይዳ ይኖረዋል፡፡
ኢትዮጵያም በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ዘርፍ በመታገዝ ስትራቴጂውን እውን ለማድረግ ጥረት እያደረገች ትገኛለች።
በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚን እውን ለማድረግ የተጀመሩ ስራዎችን በማጠናከር የወጣቱን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተሰራ ይገኛል፡፡
መንግስተ ዲጂታል ኢኮኖሚን ይበልጥ ለማሳደግ ተግዳሮት የሆኑ ጉዳዮችን በተለይም የኢንተርኔት ተደራሽነት እና ፍጥነት በሁሉም አካባቢ እኩል አለመሆን የዲጂታል ክህሎት እጥረት፣ የመሠረተ ልማት እና የኤሌክትሪክ አቅርቦት የመሳሰሉ ችግሮችን በመፍታት ዘርፉን ለማሳደግ በትኩረት እየሰራ ነው፡፡
በአቤል ነዋይ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.