Fana: At a Speed of Life!

በየዘርፉ ስብራቶችን የሚጠግኑ ኢኒሼቲቮች እየተተገበሩ ነው – አቶ አሻድሊ ሀሰን

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን በየዘርፉ ስብራቶችን የሚጠግኑ ኢኒሼቲቮች እየተተገበሩ ነው አሉ።

‎ርዕሰ መስተዳድሩ ‎በክልሉ ሶስተኛ የሆነው የባምባሲ- መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መርቀው ወደ ስራ አስገብተዋል።
‎ማዕከሉ አራት የከተማ እና ሶስት የፌዴራል በድምሩ በሰባት ተቋማት የሚሰጡ 36 አገልግሎቶችን ይሰጣል።

አቶ አሻድሊ ሀሰን በወቅቱ ባስተላለፉት መልዕክት፤ የመደመር መንግሥት በመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ቀደም ሲል በአገልግሎት አሰጣጥ የነበሩ ስብራቶችን የሚጠግን ተግባር እያከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።

የመደመር መንግስት እየሠራቸው ከሚገኙ ቁልፍ ስራዎች አንዱ መሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት መሆኑንም አንስተዋል።

‎የመደመር መንግሥት በመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ቀደም ሲል በአገልግሎት አሰጣጥ የነበሩ ስብራቶችን የሚጠግን ተግባር እያከናወነ መሆኑን ጠቅሰው፤ ለሕዝብ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት በትኩረት እየተሠራ ነው ብለዋል።

ከአገልግሎት አሰጣጥ ባሻገር በየዘርፉ ስብራቶችን የሚጠግኑ ኢኒሼቲቮች እየተተገበሩ እንደሆነ መግለጻቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.