የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ (ፕ/ር) የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ሂደትን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች:- On Aug 5, 2026 98 ቡድኖች በሂደቱ ከተነጋገሩ በኋላ እያንዳንዱ የሄዱበትን ሂደት በቃለጉባኤ ይያዝና ተፈራርመው ወደሚቀጥለው ያልፋል፡፡ ወደ ስልታዊ ቡድን ሲመጡ 50 ሆነው አምስቶቹ የተወያዩበትን ለ250 የሚያቀርቡበት፤ በዛ ላይ የሚወያዩበት፤ ይሄ ቀረ የሚሏቸውን ሀሳቦች የሚያካትቱበት ነው፡፡ 10 በነበሩበት ጊዜ ያቀረቧቸው ሀሳቦች ትዝ ሲሏቸው 50 ላይ በነበሩበት ጊዜ ያቀረቧቸው ሀሳቦች በሚገባ አለመካተታቸውን ሲያስተውሉ እንደገና እንዲዳብሩ የሚያደርጉበት ነው፡፡ ሁሉም 250ዎች ማለትም 16ቱም በያሉበት ቡድን ይፈራረማሉ፡፡ ሀሳቤ ይሄ ነው፤ ወደመሃል ያመጡን ሃሳቦች ደግሞ እነኚህ ናቸው ብለው የሚግባቡባቸውን በሙሉ በየቡድኑ በተመደቡ አጠናቃሪዎች አሉ ካጠናቀቁ በኋላ ወደ 500ዎቹ ይሄዳሉ፡፡ አንዳንዶቹ ነገሮች በቶሎ የሄዱላቸው ቡድኖች አሉ እንደገና ሀሳባቸውን እያመጡ እያስተካከሉ እያዳበሩ ዛሬ ሁሉም 16ቶቹም ተፈራርመው ይጨርሳሉ ብለን እንጠብቃለን፡፡ ተፈራርመው ከጨረሱ በኋላ አንድ አጀንዳ ላይ ወደሚወያዩበት ትልቁ የ500 ጉባኤ ይሄዳሉ፡፡ የ500 ጉባኤ ሙሉ በሙሉ የሚሳካ ከሆነ ነገ ይጀምራል፤ ዛሬ የሚያድር አጀንዳ ያላቸውም ካሉ ወደሚቀጥለው ቀን ይዘዋወራል፡፡ 4 ሺዎቹ አንድ ላይ አዳራሽ ይገናኙና ስለ 500ው ሂደት ገለጻ ይደረግላቸዋል፡፡ 500ዎቹ ከተጀመረ በኋላ ሙሉውን ሂደት በደንብ የምናሳውቅ ይሆናል፡፡ ባለሙያዎች ለሁሉም መሰረታዊ እውቀት አስጨብጠዋል ብዬ አምናለሁ፤ አንዳንድ ጊዜ የዘመሙ ሁኔታዎች ሲስተዋሉ የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ እናደርጋለን፡፡ እዚህ የመጡት ለሀገር ጉዳይ ነው ለብዙ ዘመን ተቋጥረው የነበሩ ብሶቶቻቸውን፤ ችግሮቻቸውን ይዘው መጥተው በዚህ መድረክ ላይ እንዲታወቁላቸው ለማድረግ ብዙ ትግል ቢያደርጉም ትልቁ ስዕል ኢትዮጵያ መሆኗን በሚገባ ይገነዘባሉ፡፡ የተሰጣቸውን ሁሉ ይጋታሉ ብላችሁ አትጠብቁ፤ ብዙ እውቀት ከገጠር እስከ ከተማ ኢትዮጵያ ውስጥ አለ የሚጠመዘዙ አይደሉም፡፡ ሊያሳኩ የሚፈልጉት ነገር ኢትዮጵያ በተባለችው ሀገር ዙሪያ ነው፡፡ ቃለ ጉባኤ ያዦች በትልልቅ ተቋማት የሰሩ ትልቅ ልምድ ያላቸው አንቱ የተባሉ ሰዎች ናቸው፡፡ ስህተቶችን ከስር ከስር እየተከታተልን የምናርም ነው የሚሆነው፤ ምክክር ሂደት ነው፤ ይሄ ምክክር ለሀገራችን የመጀመሪያ ነው፡፡ ምንም ቢሆን አንዳችን ሌሎቻችን ላይ ጫና መፍጠር የለብንም፤ ምክክር ማለት መከባበር፣ መነጋገር፣ መደማመጥና ወደ መካከል መምጣት ማለት ነው። በመልካም ፈቃዱ 98 Share FacebookTwitterTelegramWhatsAppEmailViberPrint