Fana: At a Speed of Life!

አዲሱ የመንግሥት ምስረታና የኢትዮጵያ ተስፋዎች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በቀደሙት ጊዜያት የተለያዩ ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ቀውሶችን ስታስተናግድ እዚህ ደርሳለች፡፡ ነገር ግን ይህ ዓመት ከሌሎቹ የተለየ እና የተስፋ ዓመት ነው፡፡
7ኛው ጠቅላላ ምርጫ 42 የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ 10 ሺህ 438 ዕጩዎች እንዲሁም ከ54 ሚሊየን በላይ መራጮች ተሳትፈው በስኬት ተጠናቅቋል፡፡
ጠቅላላ ምርጫው ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ ፍትሃዊና ተዓማኒነት ባለው ሁኔታ በስኬት መጠናቀቁ ይታወሳል፡፡
ይህን ዓመት ልዩ የሚያደርገው የመንግሥት ምስረታ የሚካሄድበት በመሆኑ ብቻ ሳይሆን፤ ለዘመናት በኢትዮጵያ ምድር የተፈጠሩ አለመግባባቶችን ለመፍታት የሀገራዊ ምክክር የተካሄደበት ዓመት በመሆኑ ጭምር ነው፡፡
ታዲያ ይህን ዓመት የተስፋ ያደረገው ኢትዮጵያ ችግሮቿን ለይታ መፍትሄ ያዘጋጀችበት ዓመት በመሆኑ ነው፡፡
ከመላው ኢትዮጵያ ተሰብስበው በአንድ የምክክር ጠረጴዛ ላይ የመፍትሄ ሀሳብ የቀረበባቸው አጀንዳዎች በኢትዮጵያ ያሉ የፖለቲካ እና ማህበራዊ አለመግባባቶችን ይፈታሉ ተብለው የተቀመጡ እና ተስፋ የተጣለባቸው ናቸው፡፡
ኢትዮጵያ አዲሱን 2019 ዓ.ም በአዲስ የመንግሥት ምስረታ፣ በአዲስ የእድገት ተስፋ፣ በአዲስ የስራ ተነሳሽነት፣ በአዲስ የቴክኖሎጂ እድገት፣ በአዲስ የስራ ፈጠራ፣ በአዲስ የመፍትሄ ሃሳቦች እና በአዲስ የአገልግሎት መሻሻሎች ነው የተቀበለችው፡፡
ይህ ዓመት ካለፈው ዓመት የተሻለ በየዘርፉ ለውጥ የሚታይበት እንደሆነ ጅማሮው አመላካች ነው፡፡
በመሆኑም የኢትዮጵያ 2019 ዓ.ም ከአዲስ የመንግሥት ምስረታ ባለፈ ሌሎችም አዳዲስ ተስፋ ሰጪ ተግባራት የሚከወኑበት ዓመት ነው፡፡
መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም የአዲሱ መንግሥት ምሥረታ የሚካሄድ ሲሆን፤ ለመርሐ ግብሩ አስፈላጊ ዝግጅቶች ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያም ለነገው ትውልድ የሚሆናትን መሰረት የምትጥልበት እድገቷን አስቀጥላ የምትሻውን እድገት ለማስመዝገብ ጉዞዋን የምታፋጥንበት ዓመት ነው፡፡
በእመቤት ሲሳይ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.