Fana: At a Speed of Life!

የቡና ምርታማነትን በሔክታር ከ9 ኩንታል ወደ 21 ኩንታል ለማሳደግ እየተሰራ ነው ‎

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሀገራዊ የቡና ምርትና ምርታማነት ኢኒሼቲቭ የቡና ምርታማነትን በሔክታር ከ9 ኩንታል ወደ 21 ኩንታል ለማሳደግ እየተሰራ ነው አሉ የግብርና ሚኒስትር አዲሱ አረጋ፡፡

ሚኒስትሩ እንዳሉት ÷ ኢትዮጵያ የቡና መገኛ ብቻ ሳትሆን ቡና የኢኮኖሚዋ፣ የሚሊየን አርሶ አደሮች የኑሮ መሠረትና የወጪ ንግዷ ዋነኛ ምሰሶ ነው፡፡

‎ይህን ታላቅ ሃብት በምርታማነት፣ በጥራትና በዘላቂነት በማሳደግ ከምርት ወደ እሴት፣ ከእሴት ወደ ዓለም ገበያ ማሸጋገር የቡና ዘርፉ ዋነኛ አቅጣጫ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

አዲሱ የቡና ልማት ፓኬጅ ከዘልማዳዊ አሰራር ወደ ዘመነ ምርታማነት መሸጋገርን የተገበረ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡

‎ለዚህም የ10 ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ ተዘጋጅቶና የቡና ልማት ፓኬጅ ተሻሽሎ በዘመናዊ የአመራረት ሥርዓት እንዲተገበር መደረጉ ጠቅሰዋል፡፡

በዚህ መሰረትም የቡና ምርታማነትን በሔክታር ከ9 ኩንታል ወደ 21 ለማሳደግ እየተሰራ ነው ያሉት ሚኒስትሩ÷ ለዚህም ከ1 ነጠብ 15 ሚሊየን ሄክታር በላይ የቡና ልማት ለማካሄድ ሥራ መጀመሩን አመልክተዋል፡፡

እቅዱን ለመተግበርም ምርጥ የቡና ዘርን መጠቀም፣ የተቀናጀ የተባይ መከላከል፣ የተቀናጀ የመስኖና የማዳበሪያ አጠቃቀምና የተሻሻለ የምርት አሰባሰብና አዘገጃጀትን ጨምሮ 9 የቡና ልማት የትኩረት አቅጣጫዎች መለየታቸውን ነው የገለጹት፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.