በዘንድሮው ኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ ከ57 ቢሊየን ብር በላይ የግብይት ስምምነት ተፈረመ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ2018 በኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ ላይ ከ57 ቢሊየን ብር በላይ የግብይት ትስስር ስምምነት መፈራረም ተችሏል አለ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር።
ሚኒስቴሩ በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ 121 መድረኮች፣ 243 ኤግዝቢሽን እና ባዛሮች ተካሂደዋል ብሏል።
በዚህም ከ57 ቢሊየን ብር በላይ የግብይት ትስስር ስምምነት መፈራረም መቻሉን አስታውቋል።
በበጀት ዓመቱ በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች በኢንዱስትሪው ዘርፍ ከተለዩ 3 ሺህ 865 ክፍተቶች መካከል 3 ሺህ 171 የሚሆኑት መፈታት መቻላቸውን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለፋና ዲጂታል የላከው መረጃ ያመላክታል።