ኢትዮጵያ የ2028ቱን የአፍሪካ ዋንጫ ለማስተናገድ ለካፍ ጥያቄ አቀረበች
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ የ2028ቱን የአፍሪካ ዋንጫ ለማስተናገድ ጥያቄዋን ያቀረበችበትን ሰነድ ለአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) አስገብታለች፡፡
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከኢፌዴሪ መንግሥት ጋር በጋራ አስፈላጊ ሰነዶችን ያካተተ ዶክመንት ለካፍ ማስገባቱን አስታውቋል፡፡
በዚህም ኢትዮጵያ ትልቁን አህጉራዊ የእግር ኳስ ድግስ ለ4ኛ ጊዜ በስኬት ለማስተናገድና በአፍሪካ እግር ኳስ ያላትን ጉልህ ታሪክ ዳግም ለማደስ ዝግጁነቷን አረጋግጣለች።