የታይላንድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አዲስ አበባ ገቡ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የታይላንድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሲሃሳክ ፉዋንግኬትክየው ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል።
የታይላንድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሲሃሳክ ፉዋንግኬትክየው ለይፋዊ የስራ ጉብኝት እና ታሪካዊውን “የታይላንድ-አፍሪካ ኢኒሼቲቭ” በይፋ ለማስጀመር ነው አዲስ አበባ የገቡት።
ሚኒስትሩ ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአዲስ አበባ ቆይታቸው ከመንግስት ከፍተኛ አመራሮች ጋር በሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ዙሪያ ውይይት አንደሚያደርጉም ተገልጿል።
ይህ ጉብኝት በኢትዮጵያ እና በታይላንድ መካከል እያደገ የመጣውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግርና የአፍሪካ-ታይላንድ ትብብርን የሚያጠናክር አዲስ ምዕራፍ ስለመሆኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመልክቷል።