የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን 12 ነጥብ 5 ቢልየን ብር ገቢ አገኘ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ2018 በጀት ዓመት 12 ነጥብ 5 ቢልየን ብር ገቢ ማግኘት ተችሏል አለ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን።
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ የኮርፖሬሽኑን የ2018 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም ዙሪያ ግምገማ አካሂዷል።
በግምገማ መድረኩ ላይ ኮርፖሬሽኑ በዓመታዊ ገቢ፣ በኪራይ ቤቶች ምደባ፣ ጥገና እና የውጭ ምንዛሬ ግኝት ከፍተኛ አፈጻጸም ማስመዝገቡ ተነስቷል።
በዚህም ኮርፖሬሽኑ በበጀት ዓመቱ 12 ነጥብ 5 ቢልየን ብር ገቢ በማግኘት የእቅዱን 91 በመቶ ማሳካቱን ለፋና ዲጂታል በላከው መረጃ አመልክቷል።
ኮርፖሬሽኑ በቀጣይ የንብረት አያያዝና አስተዳደርን ይበልጥ ማዘመን፣ ለትልልቅ ግንባታዎችና ልማቶች የሚሆኑ አዳዲስ የፋይናንስ ምንጮችን መፈለግ ላይ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራም አሳዉቋል።