Fana: At a Speed of Life!

በወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት የክልሎችን ህዝባዊ ትስስር ማጠናከር

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የተወጣጡ ወሰን ተሻጋሪ ወጣቶች በሲዳማ ክልል የተለያዩ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶችን አከናውነዋል።
በበጎ ፍቃድ አገልግሎቱ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶችና በጎ ፈቃድ ኮሚሽነር ማርቆስ ማቴዎስ ጨምሮ ከ60 በላይ ወሰን ተሻጋሪ ወጣቶች ተሳትፈዋል።
በመርሃ ግብሩ ወጣቶቹ ደም የመለገስ፣ የጽዳት ሥራዎችን የማካሄድ፣ ለአረጋውያን የምግብ ድጋፍ የማድረግ እና ለተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁሶች ድጋፍ ተግባራት አከናውነዋል።
በተጨማሪም ወጣቶቹ በሐዋሳ ከተማ በሚገኘው አዳሪ ሆስፒታል የሚገኙ ህሙማንን በመጎብኘት አጋርነታቸውን ማሳየታቸውን የክልሉ ኮሚኒኬሽን መረጃ ያመለክታል።
የዚህ ወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ዋና ዓላማ የወጣቶችን የበጎ ፈቃደኝነት ባህል በማዳበር በክልሎች መካከል ያለውን ህዝባዊ ትስስር ማጠናከር እና የወንድማማችነት መንፈስን ማሳደግ እንደሆነ ተጠቁሟል።
በሲዳማ ክልል የተከናወነው የበጎ ፍቃድ አገልግሎት “በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ፣ የተጋመደ ማንነት፣ የማይለያይ ሕዝብ” በሚል መሪ ቃል በመተግበር ላይ ባለው የበጎ ፈቃድ ንቅናቄ መርሃ ግብር አካል ነው።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.