Fana: At a Speed of Life!

‎የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አዳዲስ ኢንዱስትሪዎች ወደ ሥራ እንዲገቡ ዕድል ፈጥሯል – አቶ አሻድሊ ሀሰን


አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በርካታ አዳዲስ ኢንዱስትሪዎች ወደ ሥራ እንዲገቡ ዕድል ፈጥሯል አሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን ።

‎በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል “ከመሸመት ወደ ማምረት” በሚል መሪ ሀሳብ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ጷጉሜ 1/2018 ዓ.ም የሚቆይ “ኢትዮጵያ ታምርት” ኤክስፖ ተከፍቷል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ የመደመር መንግሥት የሀገርን ኢኮኖሚ በጠንካራ መሠረት ላይ ለመትከል እየሠራ ነው።
‌‎
‎ክልሉ የግብርናውን ዘርፍ ጨምሮ ለኢንዱስትሪ ግብአት የሚሆን ሰፊ አቅም እንዳለው ጠቅሰው፥ የአምራች ኢንዱስትሪዎች ምርትና ምርታማነትን ከጥራት ጋር ለማሳደግ በትኩረት እየተሠራ እንደሚገኝ አንስተዋል።

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የሀገር ውስጥ ተኪ ምርቶችን በማበረታታት ረገድ ትልቅ ሚና እየተጫወተ መሆኑን አንስተው፤ በክልሉ የነባር ኢንዱስትሪዎችን ምርት ከማስተዋወቅ ባለፈ በርካታ አዳዲስ ኢንዱስትሪዎች ወደ ሥራ እንዲገቡ‎ እድል ፈጥሯል ብለዋል፡፡

ኤክስፖው የክልሉን ዘርፈ ብዙ አቅሞች ለማስተዋወቅ ትልቅ ዕድል እንደሚፈጥር መናገራቸውን የክልሉ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመለክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.