Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮ ቴሌኮም በሀረሪ ክልል ለተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ጳጉሜን 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም በሀረሪ ክልል ለሚገኙ አነስተኛ ገቢ ያላቸው ነዋሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።
የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌቱ ነገዎ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ የተደረገው ድጋፍ ተማሪዎች በኢኮኖሚ ችግር ምክንያት ከትምህርት ገበታ እንዳይቀሩ ለማድረግና የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት የሚያግዝ ነው።
የኢትዮ ቴሌኮም የማዕከላዊ ምስራቅ ሪጅን ዳይሬክተር አቶ ቸሩ ጅማ በበኩላቸው፤ ተቋሙ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት በበጀት ዓመቱ ከ492 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ማድረጉን ገልጸዋል።
ሪጅኑ በክልሉ ከተማና ገጠር በሚገኙ 13 ትምህርት ቤቶች ለሚማሩ 800 ችግረኛ ተማሪዎች የደብተርና የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ያደረገ ሲሆን፤ በሪጅኑ ለትምህርት ዘርፍ ከ2 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ማድረጉ ተገልጿል።
በተሾመ ሀይሉ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.