Fana: At a Speed of Life!

 ከሀገራዊ ምክክር ጉባኤው የተገኙ ምክረ-ሃሳቦች  በየፈርጁ እየተደራጁ ነው -የምክክር ኮሚሽን

አዲስ አበባ፣ጳጉሜን 2 2018 (ኤፍ ኤም ) ከሀገራዊ ምክክር ጉባኤው የተገኙ ምክረሃሳቦች በየፈርጁ እየተደራጁ ነው አለ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

የኮሚሽኑ መግለጫ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል

 ኮሚሽኑ ከሀገራዊ ምክክር ጉባኤው የተገኙ ምክረሃሳቦችን በየፈርጁ በማደራጀት ላይ ይገኛል

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከሐምሌ 01 ቀንነሐሴ 16 ቀን 2018 . ድረስ የሀገራዊ ምክክር ጉባኤውን ሲያስተባብር መቆየቱ የሚታወስ ነው፡፡ በዚህ ሂደት ኮሚሽኑ በርካታ ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸውን ምክረሃሳቦች ማሰባሰብ የቻለ ሲሆን ይህም ኢትዮጵያዊያን በሀገራቸው ጉዳይ ላይ ለመመካከር ያሳዩት ቁርጠኝነት ውጤት ነው፡፡

 

ኮሚሽኑ በአዋጅ ቁጥር 1265/2014 አንቀፅ 9 (10 11 12) በተሰጠው ሥልጣንና ኃላፊነት መሠረት

Description: 👉የሀገራዊ ምክክር ጉባዔ አጀንዳዎችን፣ የምክክሮቹን ሂደት፣ በምክክሮቹ የተገኙ ምክረሃሳቦችን እንዲሁም ምክረሃሳቦቹ በተግባር ላይ ሊውሉ የሚችሉበትን ሥልት የሚገልጽ ሰነድ በማዘጋጀት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ለአስፈጻሚ አካሉ እና ለሌሎች የሚመለከታቸዉ የመንግስት አካላት አቅርቦ፤ ለሕዝብም ይፋ እንደሚያደርግ፤

 

Description: 👉መንግሥት ከሀገራዊ ውይይቶች የሚገኙ ምክረሃሳቦችን በተግባር ላይ ለማዋል እንዲችል ግልፅ እና ተጨባጭ የሆነ ዕቅድ እንዲዘጋጅ አስፈላጊውን እገዛ እንደሚያደርግ፤ እንዲሁም

Description: 👉የምክረሃሳቦቹን አፈፃፀም መከታተል የሚያስችል ሥርዓት እንደሚዘረጋ በአዋጁ ተደንግጓል፡፡

 

ይህንን መነሻ በማድረግ ኮሚሽኑ፦

Description: 👉በአሁኑ ሰዓት ከሀገራዊ ምክክር ጉባኤው የተገኙ ምክረሃሳቦችን በየፈርጁ በማደራጀት ላይ ይገኛል፤

Description: 👉በቀጣይ ምክረሃሳቦቹን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያቀርባል፣

Description: 👉በመቀጠልም ምክረሃሳቦቹን አግባብነት ባለው መንገድ ለሕዝብ ይፋ ያደርጋል፣

Description: 👉በመጨረሻም ምክረሃሳቦቹን ለአስፈፃሚ በማቅረብ ተፈፃሚነታቸውን ይከታተላል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.