Fana: At a Speed of Life!

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ለ487 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የ2019 ዘመን መለወጫ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለ487 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ አድርጓል፡፡

ታራሚዎቹ በመደበኛ ፍርድ ቤት በወንጀል ጉዳይ እስራት ተፈርዶባቸው በማረሚያ ቤት በመታረም ላይ የነበሩ ናቸው፡፡

ይቅርታ የተደረገላቸው ታራሚዎች በማረሚያ ቆይታቸው መልካም ሥነ ምግባር ያሳዩ፣ ለፈጸሙት የወንጀል ድርጊት የተጸጸቱና ከተጎጂዎች ጋር እርቅ የፈጸሙ መሆናቸው ተጠቅሷል፡፡

ከታራሚዎቹ መካከል 484ቱ በሙሉ ይቅርታ ከእስር እንዲፈቱ የተወሰነ ሲሆን÷ 3 ታራሚዎች ደግሞ ከዕድሜ ልክ ጽኑ እስራት ወደ 25 ዓመት እስራት ዝቅ ተደርጎላቸዋል።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው÷ ሕብረተሰቡ ታራሚዎቹ ወደ አካባቢያቸው ሲመለሱ ተገቢውን ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ጠይቀዋል፡፡

ታራሚዎች ወደሚኖሩበት ማኅበረሰብ ሲቀላቀሉ በመልካም ሥነ ምግባራቸው አርአያ በመሆን ማኅበረሰቡን መካስ እንዳለባቸው ማሳሰባቸውንም የክልሉ ኮሙኒኬሽን ለፋና ዲጂታል ገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.