ተጠባቂው ፋና ላምሮት በነገው ዕለት
አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በተወዳዳሪዎች አስደናቂ ብቃት የጀመረው ፋና ላምሮት ምዕራፍ 23 የዘጠነኛ ሳምንት ውድድር ነገ ቅዳሜ መስከረም 9 ቀን 2019 ዓ.ም ቀጥሎ ይካሄዳል።
ላለፉት ሁለት ወራት በ2 ምድብ ተከፍለው ሲወዳደሩ የቆዩት የፋና ላምሮት የምዕራፍ 23 ምርጦች ነገ ቅዳሜ ስምንት ሆነው ይገናኛሉ፡፡
ከከባድ የውድድር ሳምንታት አንዱ በሆነው በቅዳሜው ውድድር ሀይለኢየሱስ ታደገ፣ ሀይለማርያም ተገኑ፣ ሀና ተስፋዬ፣ በረከት መስፍን፣ ያሬድ ወንድምነህ፣ ዳዊት አታላይ፣ በእምነት የሽዋስ እና አማኑኤል ሙሉሀብት በቀጥታ ሥርጭት ውድድራቸውን ያደርጋሉ።
የዕለት አቀራረብ ላይ መሰረት የሚያደርገው የፋና ላምሮት ውድድር በዳኞች እና በተመልካቾች ድምፅ በየሳምንቱ አንድ ተሰናባች ይኖረዋል።
ይህን ደማቅ የምዕራፍ 23 ዘጠነኛ ሳምንት ውድድር በቀጥታ ሥርጭት በነገው ዕለት ቅዳሜ ከ6 ሰዓት ጀምሮ በሁሉም የፋና አማራጮች ይከታተሉ፡፡