“ሲምቦ ፋና” በ2018 ምርጥ የቴሌቪዥን የጉዞ ፕሮግራም ዕጩ ዝርዝር ውስጥ ተካተተ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን አፋን ኦሮሞ መዝናኛ ክፍል የሚዘጋጀው “ሲምቦ ፋና” የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን ባዘጋጀው የ2018 ምርጥ የቴሌቪዥን የጉዞ ፕሮግራም ውድድር በእጩነት ተካትቷል።
“ሲምቦ ፋና” (Simboon Faanaa) የቴሌቪዥን ፕሮግራም በኦሮሞ ሕዝብ እና በኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦች ባህል፣ ታሪክ እና ወጎች ላይ የሚያተኩር ነው።
ፕሮግራሙ በየሳምንቱ ቅዳሜ ከ11፡00 እስከ ምሽት 1፡00 ሰዓት በፋና ቴሌቪዥን ይተላለፋል።
የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽንም በፕሮግራሙ ለተሰሩ ሥራዎች እውቅና በመስጠት የሲምቦ ፋና ፕሮግራምን የ2018 ምርጥ የቴሌቪዥን የጉዞ ፕሮግራም በሚል ዘርፍ ለሽልማት በእጩነት አካትቶታል።
እርስዎም ይህንን ድንቅ ፕሮግራም ቀጣዩን ሊንክ በመጫን ድምጽ መስጠት ይችላሉ።
ድምጽ ለመስጠት ሊንኩን ይጫኑ፦ https://vote.visitoromia.org/best-travel-tv-show-of-2026/simboo-fmc
vote.visitoromia.org
Visit Oromia Traveler’s Choice Awards
Vote for Oromia’s leading tourism experiences in the 2026 Traveler’s Choice Awards.