ማንቼስተር ዩናይትድና ፉልሃም አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በ5ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚር ሊግ መርሐ ግብር ማንቼስተር ዩናይትድ ከፉልሃም ጋር 1 አቻ ተለያይቷል፡፡
ምሽት 12:30 በክራቫን ኮቴጅ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ፉልሃም ሊሳንድሮ ማርቲኔዝ በራሱ ላይ በስቆጠራት ግብ መምራት ችሎ ነበር፡፡
ይሁን እንጂ ማቲያስ ኩኛ በጨዋታው መገባደጃ ላይ ባስቆጠራት ግብ ማንቼስተር ዩናይትድ ነጥብ ተጋርቷል፡፡