Fana: At a Speed of Life!

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከ12 ሺህ ኪሎ ግራም በላይ ወርቅ ለማምረት

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በ2019 በጀት ዓመት 12 ሺህ 928 ኪሎ ግራም ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ለማስገባት በቅንጅት እየተሰራ ነው፡፡
የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ መለሰ በየነ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ በክልሉ ከወርቅ በተጨማሪ የድንጋይ ከሰል፣ የእምነበረድ እና ግራናይት ማዕድናት በጥናት ተለይተዋል፡፡
የወርቅ ምርትን ለማሳደግ እስካሁን የነበሩትን የወርቅ ማውጫ ቦታዎች ከማሻሻል ባለፈ አዳዲስ የወርቅ ማዕድን ማውጫ ቦታዎች መለየታቸውን ተናግረዋል፡፡
በዚህም በበጀት ዓመቱ በ2018 ዓ.ም የነበረውን 9 ሺህ 961 ኪሎ ግራም የወርቅ ምርት ወደ 12 ሺህ 928 ኪሎ ግራም ለማሳደግ ታቅዶ በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
እቅዱን ለማሳካት የክልሉን ርዕሰ መስተዳድር ጨምሮ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን፣ የማዕድን ቢሮ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በቅንጅት እየሰሩ ይገኛሉ ነው ያሉት፡፡
በዘርፉ የሚስተዋሉ ሕገ ወጥ ንግዶችና አሠራሮችን ለመከላከል የተጀመረው የቁጥጥር ሥራ እንደሚጠናከርም ኃላፊው አረጋግጠዋል፡፡
በእመቤት ሲሳይ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.