Fana: At a Speed of Life!

በጃፓን 2 ሚሊየን ሰዎችን ያፈናቀለው አውሎ ንፋስ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ጃፓን በታሪኳ አይታው የማታውቀውን ከፍተኛ ዝናብ እና አውሎ ንፋስ እያስተናገደች ሲሆን፣ ይህ አውሎ ንፋስ እና ዝናብ የመሬት መንሸራተቶችን እያስከተለ ይገኛል።

የአውሎ ንፋሱ አደገኛ ተፅዕኖ በሀገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች ላይ ማረፍ ጀምሯል ተብሏል።

የጃፓን ሚቲዮሮሎጂ ኤጀንሲ በአውሎ ንፋሱ ምክንያት በዜጎች ላይ አደጋ መጋረጡን በማስጠንቀቁ፣ 2 ሚሊየን የሚጠጉ ዜጎች አካባቢያቸውን ለቀው እንዲወጡ ጥብቅ ትዕዛዝ ተሰጥቷል።

የአውሎ ንፋሱ ማዕበል በዮኮሱካ ከተማ ባደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ አንድ 60 ዓመት አዛውንት ጉዳት ደርሶባቸዋል ሲል የዘገበው ቢቢሲ ነው።

የቶኪዮ የኤሌክትሪክ ኃይል ኩባንያ ባወጣው መረጃ፣ ከ50 ሺህ በላይ አፓርታማዎች እና መኖሪያ ቤቶች የኤሌክትሪክ አቅርቦታቸው ሙሉ በሙሉ ተቋርጧል።

በመቶዎች የሚቆጠሩ ዓለም አቀፍ እና የሀገር ውስጥ በረራዎች፣ የፈጣን ባቡር አገልግሎቶች ተሰርዘዋል፤ የሙዚቃ ኮንሰርቶች እና በእስያ ጨዋታዎች ስር ይካሄዱ የነበሩ የስፖርታዊ ውድድሮች በሙሉ ተራዝመዋል።

የተፈጥሮ አደጋው የሚያደርሰውን ጉዳት በቅርበት ለመከታተል ሲሉ፣ የጃፓኗ ጠቅላይ ሚኒስትር ወደ አሜሪካ ሊያደርጉት የነበረውን ይፋዊ የሥራ ጉብኝት አራዝመዋል ፡፡

አውሎ ንፋሱ በከፍተኛ ኤልኒኖ ምክንያት እንደተነሳ እና የንፋሱ ፍጥነት በሰዓት እስከ 130 ኪሎ ሜትር እንደሚደርስ ተገልጿል።

በእመቤት ሲሳይ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.