አቶ ጌታቸው ረዳ ከተባበሩት መንግሥታት የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ረዳት ፀሐፊ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ረዳት ፀሐፊ ጂን ፒየር ላክሩዋ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸው ሁለቱ ወገኖች በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን በትብብር መሥራት አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት መስጠታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡
በዚህ ወቅት ጂን ፒየር ላክሩዋ÷ ኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰላም ማስከበር ተልዕኮ፣ በተለይም በደቡብ ሱዳን ሰላም እንዲሰፍን ለማድረግ ያደረገችውን ጥረት አድንቀዋል፡፡