Fana: At a Speed of Life!

የኢሬቻ በዓል በጅቡቲ በድምቀት ተከበረ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣2019 የኢሬቻ በዓል ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች በተገኙበት በጅቡቲ በድምቀት ተከብሯል።
በበዓሉ ላይ የተገኙት በጅቡቲ የኢፌዴሪ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ኢሬቻ ክረምቱን በሰላም አሳልፎ ወደ ብራው ላደረሰን ፈጣሪ ምስጋና የምናቀርብበት እንዲሁም ለመጻዒው ጊዜ መልካሙን የምንመኝበት በዓል ነው ብለዋል።
አምባሳደሩ አክለውም በዓሉ ታናናሾች ለታላቆቻቸው አክብሮትን የሚያሳዩበት እና ስነ ምግባርን የሚያስተምር ነው ብለዋል።
“በዓሉን ስናከብር አንድነታችንን ይበልጥ ልናጠናክር እንደሚገባ እንዲሁም ሀገራችን የነደፈቻቸው ትልሞች ዕውን እንዲሆኑ መረባረብ አለብን” ሲሉ አስገንዝበዋል።
የበዓሉ ተሳታፊዎች ወደ ባሕር ዳርቻ በመውረድ ለፈጣሪ ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን፣ ባህላዊ ሙዚቃ ዝግጅትና ባህላዊ ምግቦች ጭምር የቀረቡበት መሆኑን በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.