ሀይማኖቶች የተገነቡበት መንፈሳዊ እሴት ለሀገረ መንግሥት ግንባታ እጅግ አስፈላጊ ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ሀይማኖቶች የተገነቡበት መንፈሳዊ እሴት ለሀገረ መንግሥት ግንባታ አስፈላጊ ነው አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአዲሱ የመደመር መንግሥት ምሥረታ እና የኢፌዴሪ 7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመስረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ንግግር አድርገዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሀይማኖት፣ የሲቪክ እና የባህል ተቋማት እሴት ለኢትዮጵያ ሥልጣኔ ተገቢውን ሚና እንዲጫወቱ ምቹ ሁኔታ ይፈጠራል ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) አክለውም የተቋማቱ እሴት “ሙስናን፣ ብልሹ አሰራርን እና ከሥነ ምግባር የወጡ አካሄዶችን ለማረቅ ፍቱን መድኃኒት ነው፤ በሕዝቦች መካከል ወገን ዘለል ትስስር ለመፍጠርም አቅም አለው” ብለዋል።
የሲቪክ ተቋማት በሀገር ፍቅር መንፈስ ተቃኝተው፣ ሲቪክ ማንነት በመገንባት ረገድ እስካሁን ከሰሩት የላቀ ሚና እንዲጫወቱም አሳስበዋል፡፡
በቴዎድሮስ ሳህለ